NOMINATION

ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ

ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ዕጩ ጥቆማ ማቅረቢያ 

ለደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ዕጩዎች ስለመጠቆም የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SSB/62/2015 መሰረት በደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ 4ኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የተሰየመው የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ ስራውን የጀመረ ሲሆን የዕጩ ጥቆማ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለሆነም ባለአክሲዮኖች ከግንቦት 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2009ዓ.ም ድረስ ብቻ ለቦርድ አባልነት መስፈርት የሚያሟሉና ለባንኩ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን እጩዎች እንዲጠቁሙ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ለቦርድ አባልነት ምርጫ በዕጩነት የሚጠቆሙ ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርት፡-

  1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ/ች እና ቢመረጥ/ብትመረጥ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
  2. ዕድሜ 30 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
  3. በማንኛውም ባንክ ሰራተኛ ያልሆነ/ች፤
  4. የደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፤
  5. ተጠቋሚው የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን የሚወክለው የተፈጥሮ ሰው ማንነት መግለጽ የሚችል፤
  6. ቢያንስ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ/ች ወይም ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያለው/ያላት፤
  7. በቢዝነስ ማኔጅመንት በተለይም በባንክ ስራ ዘርፍ በቂ እውቀትና የስራ ልምድ ያለው/ያላት ወይም ከተመረጠ/ች በኋላ ስለባንክ ስራ ማኔጅመንት ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
  8. በሌላ ተወዳዳሪ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ በቦርድ አባልነት በማገልገል ላይ ያልሆነ/ች፤
  9. መልካም ስነ ምግባርና ማህበራዊ ተቀባይነት ያለው/ያላት በተለይም የእምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ/ች፣ ለፋይናንስ ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሀሰተኛ ማስረጃ ያልሰጠ/ች፣ የስነ ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የስነ ስርዓት እርምጃ ያልተወሰደበት/ባት፣ በሙስና ወንጀል ተከሶ/ሳ ያልተቀጣ/ች እና ከመምረጥ መመረጥ መብት ያልተገደበ/ች፤
  10. የመክሰር ውሳኔ ያልተሰጠበት/ባት እና ከታክስና ባንክ ጋር የተያያዙ ግዴታዎች በአግባቡ የተወጣ/ች፤

ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ዕጩ ጥቆማ ማቅረቢያ ፎርም