- March 9, 2021
- Posted by: admin
- Category: Sponsorship, Uncategorized
No Comments
ደቡብ ግሎባል ባንክ ይህን ከጁምዓ እስከ ሰንበት በሚል ስያሜ የተዘጋጀውን እና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳውን የነጋዴ ሴቶች የንግድ ባዛር በብቸኛ አጋርነት አዘጋጅቷል፡፡
ደቡብ ግሎባል ባንክ ባዛሩን ድጋፍ ያደረገባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች፡-
- በንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ስራቸው ጎልቶ የሚወጣበትን አጋጣሚ መፍጠር
- በኮቪድ-19ና በሌሎችም ምክንያቶች ተቀዛቅዞ የነበረው የቢዝነስ እንቅስቃሴ ላይ መነቃቃት ለመፍጠር
- ከተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት ለስኬት መሰረት በመሆኑ
- በአገር ደረጃ እየተካሔዱ ባሉ የህብረተሰቡን ሕይወት ሊለውጡ በሚችሉ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማበርከት የባንካችን የዘወትር ተግባሩ በመሆኑ
- እንደ መልዕክታችን ለሴቶች የእድገት መሰላል መሆናችንን ለማሳየት
- ሴቶችን ማገዝ የአጠቃላይ ማህበረሰቡን፣ ብሎም የአገርን እደገት ማገዝ ነው ብለን ስለምናምን
ባንካችን ለማህበራዊ ጥሪዎች ፈጣን ምላሽ መስጠቱን፣ ከማህበረሰቡ ጋር አብሮ ማደጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡


