ደቡብ ግሎባል ባንክ ከግሮቭ ጋርደን ጋር በመተባበር ሴት ነጋዴዎች ብቻ ተሳታፊ የሚሆኑበትና ለሁለት ወራት የሚቆይ የንግድ ባዛርን ስፖንሰር አደረገ

• ደቡብ ግሎባል ባንክ ይህን ከጁምዓ እስከ ሰንበት በሚል ስያሜ የተዘጋጀውን
እና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳውን የነጋዴ ሴቶች የንግድ ባዛር በብቸኛ
አጋርነት አዘጋጅቷል፡፡
• ደቡብ ግሎባል ባንክ ባዛሩን ድጋፍ ያደረገባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች፡-
o በንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ስራቸው ጎልቶ የሚወጣበትን አጋጣሚ
መፍጠር
o በኮቪድ-19ና በሌሎችም ምክንያቶች ተቀዛቅዞ የነበረው የቢዝነስ
እንቅስቃሴ ላይ መነቃቃት ለመፍጠር
o ከተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት ለስኬት
መሰረት በመሆኑ
o በአገር ደረጃ እየተካሔዱ ባሉ የህብረተሰቡን ሕይወት ሊለውጡ
በሚችሉ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን አስተዋጽዖ
ማበርከት የባንካችን የዘወትር ተግባሩ በመሆኑ
o እንደ መልዕክታችን ለሴቶች የእድገት መሰላል መሆናችንን ለማሳየት
o ሴቶችን ማገዝ የአጠቃላይ ማህበረሰቡን፣ ብሎም የአገርን እደገት ማገዝ
ነው ብለን ስለምናምን
ባንካችን ለማህበራዊ ጥሪዎች ፈጣን ምላሽ መስጠቱን፣ ከማህበረሰቡ ጋር አብሮ ማደጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡