ደቡብ ግሎባል ባንክ ከሶልጌት ጉዞ ኃ.የተ.የግ.ማ ጋር የስራ ስምምነት ውል ተፈራረመ

ደቡብ ግሎባል ባንክ እና ሶልጌት ጉዞ ኃ.የተ.የግ.ማ በጉዞጎ የሞባይል መተግበሪያ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ውል ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በጎልደን ሮያል ሆቴል የባንኩ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ዳይሬቴክተር አቶ ሲሳይ አየለ እና የጉዞጎ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በሱፈቃድ ጌታቸው በተገኙበት ተፈራርመዋል፡፡